የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ህትመት፣ የመኪና እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
አሽተሽፍቁባ/ቂርቆስ/2019/001
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ሎት 1. የደንብ ልብሶች
ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 4. የህትመት እቃዎች (ስራዎች)
ሎት 5. የመኪና ዕቃዎች
ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ ::
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት) ድረስ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል::
- የጨረታ ሰነዱን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ 1ኛ ምድር ቤት የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት) ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል የ4,000 ብር (አራት ሺህ ብር) CPO ከባንክ አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ከመስቀል አደባባይ ወደ ባምቢስ በሚወስደው መንገድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ 1ኛ ምድር ቤት የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5-58-38-71 መጠየቅ ይቻላል::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority, Kirkos Branch, seeks suppliers in 6 lots: uniforms, office consumables, cleaning items, printing, vehicle parts and electronics. Open bid.
