Tender Detail

Tender Details

  • Company South Nation Nationality of Peoples Regional State Construction Autority (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን)
  • Address አርባ ምንጭ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461810701
  • Website
  • Deadline14 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100
  • Bid Securityኤሌክትሮኒክስ 50,000፤ ፍተሻ ማሽን 160,000፤ ጽሕፈት መሣሪያ 25,000፤ ጽዳት 10,000 ብር (CPO ወይም ካሽ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከሰዓት 8:00 ሰዓት
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Laboratory Equipment And Chemicals , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን፣ የጽሕፈት መሣሪያና የፅዳት ዕቃዎች ግዥ

South Nation Nationality of Peoples Regional State Construction Autority (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክ፣ የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን ፣ የጽሕፈት መሣሪያ እና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ::

  • ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  • በገቢዎች ባለሥልጣን የምዝገባ ሠርተፍኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት/15/ የሥራ ቀናት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን በአካል በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት ለኤሌክትሮኒክስ እና የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን ጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የጽሕፈት መሣሪያና ጽዳት ዕቃዎችን ጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአስራ አምስተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
  • ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ 50,000.00 (ሃምሣ ሺህ ብር) የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማሽን 160,000.00 /አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ ለጽሕፈት መሣሪያ 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለጽዳት ዕቃዎች 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በካሽ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  • ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ብቻ መጠቀም አለባቸው::
  • የጨረታው አሸናፊ ጨረታ ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት::
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አርባ ምንጭ
የቢሮ ስልክ ቁጥር 04618107051

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional State Construction Authority in Arba Minch seeks suppliers of electronics, a construction material quality testing machine, stationery and cleaning materials. Open bid.
Save Tender