Tender Detail

Tender Details

  • Company Arba Minch Polytechnic and Satellite Institute (የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት)
  • Address አርባ ምንጭ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0468810960
  • Websitehttps://www.amtvet.edu.et/
  • Deadline10 Nov 2026, 1:15 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር
  • opening dateበቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Educational And Training Equipment And Machinery , Electrical/Electronics Educational And Training Equipment

የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የሥልጠና መሣሪያዎች፣ የጽሕፈትና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ጨረታ

Arba Minch Polytechnic and Satellite Institute (የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት)


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ. ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በ2019ዓ.ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የመደበኛ እና የካፒታል በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ማለትም ለቴክስታይል እና ጋርመንት፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለኮንስትራክሽን ሥራ፣ ለማሽን፣ ለሜካኒክስ፣ ለኤሌክትሮ ቴክኖሎጅ (ለባዮ ሜዲካል) ዲፓርትመንቶች ለሥልጠና፣ አገልግሎት የሚውል ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ የሥልጠና መሣሪያዎች፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች የቲን ቁጥር /tin Number/ ያለው /ያላት
  2. በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  3. የዕቃውን ዋጋ በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ገፁን ሳይገነጣጥል ሞልቶ የሚያቀርብ
  4. የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎች መለያ /specification/ ኮሌጁ ባዘጋጀው መሠረት ብቻ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣
  5. የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብና ማስያዝ ይገባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን / Bid Document/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ/ም/ቅ ፖ/ቴ/ሳ/ ኢንስቲትዩት ከ/ሂ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን ፣ ማህተምና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
  9. አጠቃላይ የማስረጃቸውን ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል የሚል ማህተም አርፎበት እና ተፈርሞበት ተያይዞ መቅረብ አለበት።
  10. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሰነድ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ የዕቃው ነጠላ ዋጋ በአንድ ላይ በታሸገ ፖስታ ኢንቨሎፕ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው የሥራ ቀን ከሆነ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ሣጥን በአ/ምንጭ ፖሊ. ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ቀኑ በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል
  11. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፣ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ውጭ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም።
  12. አሸናፊዎች የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈራረም አለባቸው፣
  13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብና ማስረከብ አለበት።
  14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. የተጭበረበረ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም በሕግም ያስቀጣል።

ለተጨማሪመረጃ:- 0468810960/0910744129/0912056962 ደቡ/ብ/ኢ/ክ/መ/ሥ/ክ/ቢ/አ/ም/ፖ/ቴ/ሳ/ ኢንስቲትዩት ደውለው ይጠይቁ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት

✨ messages.ai_summary
Arba Minch Polytechnic and Satellite Institute, South Ethiopia, buys by open tender training materials for its textile, agro-processing, construction, machining, mechanics and electro-technology departments, plus electronic training equipment, stationery and cleaning items.
Save Tender