Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Education Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-2-26-62-67
  • Websitehttps://anrseb.gov.et/
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት አንድ ብር 50,000.00፣ ሎት ሁለት ብር 50,000.00፣ ሎት ሶስት ብር 150,000.00 እና ሎት አራት ብር 150,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበ11 ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በትም/ቢሮ አዳራሽ ጨረታዉ ይከፈታል።
  • Categories Textile, Garment & Leather , Personal Care Products And Services , Educational And Training Equipment And Machinery

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ ስም በዩኒሴፍ በጀት የሚገዙ እና አገልግሎት የሚውል ሎት አንድ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ሎት ሁለት የንፅህና መስጫ ሳሙና ሎት ሶስት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ ሎት አራት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Amhara National Regional State Education Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)


የግዥው መለያ ቁጥር BOE/ግፋን/11/2019

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ ስም በዩኒሴፍ በጀት የሚገዙ እና አገልግሎት የሚውል ሎት አንድ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ሎት ሁለት የንፅህና መስጫ ሳሙና ሎት ሶስት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ ሎት አራት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች:-

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
  2. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ
  4. የግዥው መጠን ብር ከ500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ።
  5. የምዝገባ የምስክር ወረቀት
  6. የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል(ለሎት 3 እና ሎት 4)
  7. የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል(ለሎት 3 እና ሎት 4)
  8. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-7 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት እና መውሰድ ይቻላል ።
  10. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ ሎት አንድ ለስልጠና የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ብር 50,000.00፣ሎት ሁለት የንፅህና መስጫ ሳሙና ብር 50,000.00፣ሎት ሶስት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል የውስጥ ሱሪ ብር 150,000.00 እና ሎት አራት ለልጃገረዶች አገልግሎት የሚውል እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ ብር 150,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ።
  12. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታዉ ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልፅ ጨረታ የሚል ተጽፎበት ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት እና በ11ኛዉ ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን መግባት ይኖርበታል።
  13. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በትም/ቢሮ አዳራሽ ጨረታዉ ይከፈታል።
  14. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  15. ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67/ በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  16. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበ ነዉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

✨ messages.ai_summary
Amhara Regional Education Bureau buys, with UNICEF funding, four lots by open tender: training inputs, hygiene soap, underwear for girls and reusable sanitary pads. Bidders need a renewed sector licence, tax clearance, TIN and registration; lots 3-4 also need competency and performance letters.
Save Tender