የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የበጀት መረጃ ቴምፕሌት ህትመት አገልግሎት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 03/2017
በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የበጀት መረጃ የሚገልፅ ቴምፕሌት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል::
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል::
- ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር300.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11:25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና/ንብ/አስ/ዳይሮክቶሬት ይከፈታል:: 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለውቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3:00 ሰዓት ተዘግቶ 3:30 ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
- የፋይናንሻል እና የተጠየቁት ህጋዊ ሰነድ እንደዚሁም ሲ.ፒ.ኦ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት ለ60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል::
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ 15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት::
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር፡- 046-180-50-71 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
✨ messages.ai_summary
South Ethiopia Regional State Finance Bureau in Wolaita Sodo seeks printers to print various budget information templates for the fiscal year. Open bid.
