የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የ2019 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ /የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ሎት 2 የተለያዩ ህትመቶች ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 የደንብ ልብሶች ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸርና ሌሎች / ሎት 7 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን/ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን / በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የ2019 በጀት አመት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ /የቢሮ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 2 የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 የደንብ ልብሶች
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸርና ሌሎች /
- ሎት 7 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን/ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን /
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN Number/ ያላቸው
- የአገልግሎት መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 13 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር መወዳደር ለሚፈልጉት እያንዳንዱ ሎት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት እስከ 6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን 6ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 4:00 የጨረታ ሰነድዎን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታውን የምናወዳድረው የጽህፈት መሳሪያን፣ህትመትን የጽዳት እቃዎችን እና የደንብ ልብሶችን በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ሲሆን ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ እቃዎችን በነጠላ ዋጋ ይሆናል።
- የዕቃውን ማንኛውንም ማጓጓዣ ወጪ ችሎ ኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፣
- የደንብ ልብስ አሸናፊው የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 28 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335511147 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kombolcha City Woreda Court buys in seven lots by open tender: stationery and office consumables, printing, cleaning items, uniforms, electronics, furniture and other fixed items, and various tools. Bidders need a renewed trade licence, paid tax, TIN and VAT for supplies over 200,000.
