የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የካፍቴሪያ እና የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ
Ethiopian Public Service University (የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን ካፍቴሪያ እና የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ አገልግሎት ሺያጭ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::
1. የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ
የካፍቴሪያ ኪራይ:
ጠቅላላ ካሬ ስፋት: 291 ካሬ ሜትር
የአገልግሎት አይነት: ለንግድ
የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ:
ጠቅላላ ካሬ ስፋት: 32 ካሬ ሜትር
የአገልግሎት አይነት: ለንግድ
2. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች
ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ቲን፣ቫት፣የንግድ ምዝገባ እና የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 202 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. አጠቃላይ መመሪያዎች
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-646-33-15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች የሚከራዩትን የካፍቴሪያ እና የወንድ ጸጉር ቤት ኪራይ አገልግሎት አስቀድመው መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የቀረበው የኪራይ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል::
አድራሻ:- አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሲ.ኤም.ሲ መንገድ (ሰአሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ)
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Public Service University is renting out, by tender, a 291 square metre cafeteria and a 32 square metre men's barbershop on its campus in Lemi Kura sub-city, Addis Ababa. Site visits are possible before bidding. Open bid.
