Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571107
  • Websitehttps://awashbank.com/am-et/
  • Deadline24 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityለጨረታው መወዳደሪያ የሚሆን የ1 (አንድ) ወር ኪራይ መነሻ ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር ስም በማሠራት
  • opening dateጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሕዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት አሰላ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአሰላ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 5(አምስት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. በአሰላ ከተማ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ ባለ 5(አምስት) ወለል ሕንፃ ለንግድ፣ ለቢሮ እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታውን መመሪያዎች በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን አሰላ ከተማ በሚገኘው አዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ በማቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለጨረታው መወዳደሪያ የሚሆን የ1 (አንድ) ወር ኪራይ መነሻ ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር ስም በማሠራት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሕዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ አሰላ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ሴኪዩሪቲ ቦንድ) ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሕዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት አሰላ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራቀናት ውስጥ የ3 ወራት የኪራይ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል ውል ሊፈፀም ይጠበቅባቸዋል፣ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን ፈጽመው የኪራይ ውል ካልፈፀሙ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-530-31-02/04፣ ወይም 022-331-28-75 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Awash Bank S.C. offers for rent, through a tender, space in its standard 5-storey building in Asella town for commercial, office and other uses. Open to interested bidders; details are in the tender document available at the Asella branch.
Save Tender