Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
  • Address ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አለፍ ብሎ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111562305
  • Website
  • Deadline20 Nov 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ልሳን (Addis Lessan)
  • Bid Document Price2,300 ETB per document (non-refundable, paid online with telebirr)
  • Bid Security50% of plot area × floor price, as CPO
  • opening dateProvisional results ህዳር 17/2019 ዓ.ም 3:00 ሰዓት (26 Nov 2026, 09:00), online
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ


Tender Documents:

የ9ኛ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ - የቦታዎች ዝርዝር (127 ቦታዎች) / Round 9 plot list

Price: Free


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ፣ የካ ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በaddislandfarm.gov.et:(https://addislandfarm.gov.et/land-auction) በኦን ላይን በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 30/2019ዓ.ም እስከ ህዳር 11/2019ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ለጨረታ የወጡ ቦታዎችን በሊዝ ለመጫራት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1.1. ተጫራቹ ጨረታዉን መሳተፍ የሚፈልገው በግል ከሆነ የጨረታ ሰነድ ግዥ የሚፈጽመው በፋይዳ መታወቂያ ቁጥር ባለው ባለ አስራ ስድስት አሃዝ የካርድ ቁጥር(FAN) ብቻ በመጠቀም ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.2. ተጫራቹ ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልገው ህጋዊ ሰዉነት ባለው ማህበር ፣ አክሲዮን ወይም ድርጅት ከሆነ የጨረታ ሰነድ ግዥ የሚፈጽመው በማህበሩ ፣ በአክሲዮኑ ወይም በድርጅቱ ስም በተከፈተው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ብቻ በመጠቀም ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ቦታውን በሲስተሙ ላይ በተቀመጠው google map አቅጣጫ ጠቋሚ(location) መሰረት በአካል መመልክት ይችላሉ፡፡በተጨማሪ በ30/02/19ዓ.ም ፣ 03/03/19ዓ.ም እና በ07/03/19 ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00ሰዓት - 6፡30ሰዓት እና ከሰዓት 8፡00 ሰዓት - 11፡30 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘዉን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ወይም በድህረ ገጹ ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወረክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር መ/ቤቱ አይጠየቅም፡፡

6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO) ብቻ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በመፃፍ ህዳር 11/2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በፖስታ አሽገው ሲያቀርቡ በፖስታው ላይ የሚጻፈው የጨረታ ቁጥርና የቦታ ኮድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው የቦታ ኮድና የጨረታ ቁጥር ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡

7. ተጫራቾች ለአንድ ካሬ ሜትር የሚሰጡትን ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተገለጸው ድረ ገጽ በመግባት በተዘጋጀው የዋጋ መስጫና የቅድመ ክፍያ መጠን በፐርሰንት በቀጥታ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡አሞላሉን በተመለከተ በዚሁ ደህረ ገጽ ላይ በተያያዘው አጭር ቪዲዮ በመታገዝ መሞላት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹ ደጋፊ ሰነዶች ጥራቱን በጠበቀ ስካነር ስካን በማድረግ ከሲስተሙ ባለው የመጫኛ ቦታ ላይ መጫን(Upload) ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡

8.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO) ከፊትና ከኃላ

8.2 የተጫራቹ ፋይዳ መታወቂያ

8.3 የቴሌ ብር ደረሰኝ

8.4 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ደብዳቤ

8.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ

8.6 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት

8.7 ጨረታውን የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

8.8 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. የጨረታ አሸናፊዎች ጊዚያዊ ውጤት ህዳር 17/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ለመሬት ሊዝ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሲስተም በኦንላይ ይፋ ይሆናል፡፡ ከጊዚያዊ ውጤት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ ጊዚያዊ ውጤቱ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በሲስተሙ በተዘጋጀው ቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

10. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የስራ ቀናት በኀ_ላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ከወጡት ውጭ ያሉ በንግድ ባንክ ፣ ዳሽን፣ አብሲኒያ እና አዋሽ ባንክ የተሰሩ ሲፒኦዎች በቢሮ በኩል ወደ ባንኮቹ ተመላሽ ይደረጋል ፡፡ በካሽ ያሰሩ እና ከላይ ከተጠቀሱት ባንኮች ውጭ ያሉ ተጫራቾች የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከላይ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም፡፡

11. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መስፍርት ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ በተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

12. መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ማሳሰቢያ

የህንጻ ከፍታና የፕላን ጉዳዮች በተመለከተ በቦታው ስፋት እና በአካባቢው ጥናት ላይ የሚመሰረት በመሆኑ ተጫራቾች የቦታውን የህንጻ ከፍታ በተመለከተ ከከተማ አስተዳደሩ የፕላን እና የግንባታ ህግ መሰረት የሚዳኝ መሆኑን አውቃችሁ እንድትወዳደሩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች (127 ቦታዎች): ኮልፌ ቀራኒዮ 10፣ ለሚ ኩራ 23፣ ቦሌ 33፣ አራዳ 2፣ አቃቂ ቃሊቲ 41፣ አዲስ ከተማ 8፣ የካ 6፣ ጉለሌ 4። የእያንዳንዱ ቦታ ኮድ፣ ስፋት፣ መነሻ ዋጋ እና የሲፒኦ መጠን በተያያዘው PDF ውስጥ ይገኛል።

Plot list (127 plots with plot code, area, floor price and CPO amount): see the attached PDF.

Source: Addis Ababa City Administration Land Development and Administration Bureau — official notice and online application at addislandfarm.gov.et. Also published in Addis Lessan, 7 November 2026.

✨ messages.ai_summary
Round 9 lease auction of development plots in eight Addis Ababa sub-cities by the city Land Development and Administration Bureau. Individuals apply with Fayda ID, companies with TIN; one plot per bidder; online application on addislandfarm.gov.et.
Save Tender