የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገኝ የንግድ ቤት የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ)
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ራሔል አለማየሁ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሰለሞን ብሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/164150 26/09/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/171271 በ03/04/2018ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/171271 በ24/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር ML/B-14/SN/004 ይዞታው ቤቱ E-ካርታ የሆነ ቤቶ በአቶሰለሞን ብሩ አየለ ስም የተመዘገበ የቤቱ ህንጻ ቁጥር 14 የወለል ቁጥር ግራውንድ (Ground) የሆነ የቤቱ ስፋት 45.63ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያ ስፋት 42.08ካ/ሜ ጠቅላላ ስፋት 87 ካ/ሜ የሆነ የቤቱ አገልግሎት የንግድ የሆነ ንግድ ቤቱ ላይ ቀሪ ያልተከፈለ ዕዳ ወለድን ጨምሮ 50% ያልተከፈሊ ዕዳ 1,184,388.50( አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስምንት ከ50/100) ያለበት ሲሆን ቤቱ በአሁኑ ሰዓት ካርታ ያልወጣለት ምክንያቱም 1ኛየፍ/ባለዕዳ እና 2ኛ ተጠባባቂ የነበሩት ግለሰብ መካከል ባለው ዕግድ ምክንያት ነው በማለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልፆልናል:: ስለዚህ የተባለው እግድ የተነሳ ስለሆነ የጨረታ አሸናፊ ለወደፊት ካርታ ሂደት ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መሃደሩ የሚደራጅለት ይሆናል:: የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,824,557 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አራት ሽህ አምስት መቶ ሃምሳ ሰባት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ [...] 8 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራቾች ባለመቅረባቸው ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.171272 በቀን ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 956,139.25 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ25/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 2 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል::የተጫራቾች ምዝገባ 5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት:: በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
