Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-122-00-20
  • Websitehttps://www.oromiaforest.et/
  • Deadline13 Nov 2026, 4:23 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateበጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Forest And Tree Sales

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቁም ደን (የፈረንጅ ጥድ፣ ባህር ዛፍ እና ድብልቅ ግንድላ) ሽያጭ

Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)


የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU-04/2019

ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት፣ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት፣ አርሲ ቅ/ጽ/ቤት እና ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፣ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ"Gravelea, roubsta" ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፣ በተጨማሪ በነዚሁ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት፣ ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፣ እንዲሁም ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፣ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ"Gravelea roubsta" ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፣ በተጨማሪ በነዚሁ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

  1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና "TIN number" ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፣ ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ጎባ ከተማ፣ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፣ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፣ ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ፊንፊኔ ከተማ፣ ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት ነጌሌ አርሲ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ::
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል::
  3. ጨረታው የምዘጋበት እና የምከፋትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል::
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 በመደወል ማጠየቅ ወይም "www.oromiaforest.et" ድረ-ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ::

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Oromia Forest and Wildlife Enterprise is selling standing forest timber (cypress, eucalyptus, Grevillea and mixed species logs) at its Jimma, Wollega, Arsi, Hararghe, Ilu Aba Bora, Bale, Borana Guji and Finfinne branches. Open to licensed sawmill operators. Open bid.
Save Tender