Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለመ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114708503
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityዕቃ ግልፅ ጨረታ: የሰጡትን ዋጋ 5% CPO፤ ዕቃና ተሽከርካሪ ሐራጅ: ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000.00 CPO (ለተወሰኑ ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ እንደተገለጸው)
  • opening date09/03/2019 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4:00 ሰዓት ይከፈታል።
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 18/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 18/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎችም የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ህዳር 03/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ከፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም:-

  1. በዕቃ ግልጽና ሀራጅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።
  2. በተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  3. በጨረታ ላይ የዕቃው ወይም የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹንና የተሽከርካሪውን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 03/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አስርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  6. በዕቃና የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጸው የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልፃለን። ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ሰኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
    ተ.ቁየቅ/ጽ/ቤቱ ስምየጨረታው አይነትየንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
    1አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤትየእቃ ሀራጅእስከ 07/03/2019እስከ 08/03/2019 (ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ) መሰረት ይካሄዳል።
    2የእቃ ሀራጅእስከ 08/03/201909/03/2019 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4:00 ሰዓት ይከፈታል።
    3የተሽከርካሪ ሐራጅእስከ 08/03/2019እስከ 09/03/2019 (ከ5:00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ) መሰረት ይካሄዳል።
  8. የጨረታው መካሄጃ ቦታ:- ሙሉ በሙሉ የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
  9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ተሽከርካሪውን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 - 05 -11 -55 -11

አድራሻ:- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (አክሽን ኢትዮጵያ)

በስልክ ቁጥር:- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ:- 011 470-85-03

አድራሻ:- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Customs Commission Addis Ababa Kality Branch sells seized and confiscated vehicles and goods as is, online via Auction Ethiopia: spare parts, mobiles, electronics, home and office items, clothing, shoes, cosmetics and more. Vehicle auctions are open to Ethiopians over 18.
Save Tender