የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት ስትገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድራ ለመሸጥ አቅርባለች።
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት ስትገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድራ ለመሸጥ አቅርባለች።
ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት በመቅረብ ብር 500 ከፍለው የጨረታ ሰነድና ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ሰዓት በአስረኛው(10ኛው) ቀን ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት ይሆናል። ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ ቃለ-ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታው ሰዓት በፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሰጡት ዋጋ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለጨረታ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቆ ንብረቱን መረከብ ይገባል። ነገር ግን ካልተረከበ ያስያዘው ገንዘብ ለቤተክርስቲያኒቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊው ይሰረዛል።
- ቤተክርስቲያኒቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቷ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:-
ስልክ ቁጥር:- 0911601035 / 0913521435
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Kale Heywet Church Head Office, Addis Ababa, sells its used vehicles by tender. Vehicles are at the head office compound, where bids are opened. Open to all interested bidders.
