Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline09 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4ኛ (በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ CPO)
  • opening dateህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም (ምዝገባ እንደተጠናቀቀ)
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ ያልተጠናቀቀ ቅይጥ አገልግሎት ቤት የሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሲምቴክ ኮንስትራክሽን እና የፍ/ባለዕዳ ደብሊው ኤፍ ኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ሀ/የተ/የግ/ማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/15835 በ21/04/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/22532 በ10/06/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ቤት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የሚገኝ የካርታ ቁጥር AA000060502196 የቦታው ስፋት 620 ካ/ሜ ያልተጠናቀቀ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 33,345,000 (ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሺ.ህ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.PO ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም c.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office is auctioning an unfinished mixed-use building on a 620 square metre plot in Bole sub-city, Woreda 05, Addis Ababa, under a court order. Bidders must deposit a quarter of the starting price by CPO. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender