መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር 132
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ቁሳቁሶቹም:-
- ቁርጥራጭ አልሙኒየም (ስክራፖች)
- ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ቱቦላሬዎች /ስክራፕ/
- ያገለገሉ ጎማዎችና የፍሬን ዘይት
- ያገለገሉ ሶፋዎች
- ያገለገሉ የስፕሪንግ ፍራሾች
- የውሃ ጀሪካኖች
- ያገለገሉ ወንበሮች
- የውሃ ታንከሮች
- ብዛት ያላቸው የኢንዶኔዥያ ምርት የሆኑ ውድ ፍሪ ወረቀቶች ባለ 80 ግራም እያንዳንዱ ሪም 500 Sheet የያዙ ወረቀቶች
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5:00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ:-
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር:- 0989-90-90-51 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
