በከሳሾች/አመልካቾች 1ኛ ሲሳይ መገርሳ፣ 2ኛ ካሚል ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው የዶሮ እርባታ ህብረት ስራ ማህበር፣ እና በተከሳሽ ናይማ ጂሃድ መካከል ስላለው ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሄር ጉዳይ ችሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
በከሳሾች/አመልካቾች 1ኛ ሲሳይ መገርሳ፣ 2ኛ ካሚል ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው የዶሮ እርባታ ህብረት ስራ ማህበር፣ እና በተከሳሽ ናይማ ጂሃድ መካከል ስላለው ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ፅ/ቤት ከሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ መሬት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወኪል፣ ከፉሪ ክፍለ ከተማ መሬት ጽህፈት ቤት፣ ከፉሪ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት እና ከፉሪ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመሆን፣ በሸገር ከተማ በፉሪ ክፍለ ከተማ ሙዳ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት፣ ወሰኑ በሰሜን-መንገድ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ በመኖሪያ ቤት የሚዋሰን፣ የቦታ ስፋቱ 211.73 ካሬ ሜትር የሆነ፣ በሰነድ ቁጥር OR0007181618022 በመልስ ሰጪ/ተከሳሽ በባለቤትነት ስም የተመዘገበውንና ግምቱ 12,199,733.57 ብር (አስራ ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ57 ሳንቲም) የሆነውን ንብረት፣ የፍርድ አፈፃፀም ክፍያን ለመፈጸም ሲባል የ12,616,450 ብር (አስራ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) በግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከ 30/02/2019 ዓ.ም እስከ 30/03/2019 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ያህል አየር ላይ ውሎ ፣ ንብረቱ በሚገኝበት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ እና ብዙ ሰዎች ሊያዩት በሚችሉበት ቦታ ተለጥፎ ተወዳዳሪዎች ሙሉ መረጃውን ከሸገር ከተማ የፋይናንስ ፅ/ቤት በመሄድ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ታውቆ፣ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 1/4ኛ (አንድ አራተኛ) የመነሻ ዋጋ በመያዝ እንዲቀርቡ በማድረግ 01/04/2019 ዓ.ም ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ከቀየ በኋላ፣ የጠቅላላ ክፍያ አፈፃፀም ግዢው ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆን ሆኖ፣ ከተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ሽያጩን በማድረግ ውጤቱን እንድታሳውቁን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ በ02/04/2019 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ተይዟል።
