Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበሎት ከ2,000 እስከ 100,000 ብር (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening date9/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት፣ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ዘይት እና ሌሎች የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


ክፍል አንድ

የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ

የመጀመሪያ ዙር የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽጨ/001/ኦኩስፋ/1 እና 3/2019

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ያገለገሉ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ የተለያዩ ያገለገለ ባለ ክር እና ባለ ሺቦ ጎማዎች ፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የተቆራረጡ ከመነዳሪዎች ፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የተሽከርካሪና የማሽነሪ ባትሪዎች ፣ ባዶ ያገለገሉ የዘይትና ግሪስ በርሜሎች ፣ ያገለገለ/የተቃጠለ ዘይት (በበርሜል) ፣ ባዶ የአፈር ማዳበሪያ ከረጢት UREA&NPS ፣ የኬሚካል ጀሪካን ባለ 1 ሊትር እና ባለ 5 ሊትር ፣ የኤሲ ጋዝ ባዶ ሲሊንደር ባለ 45 ቁጥር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ::

  1. ማንኛውም ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ስነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ:- ክልል በምእራብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እና ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ወረዳ ሳላማጎ ወረዳ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ነው ::
  3. ጨረታው በቀን 9/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል:: ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ) በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን: 9/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል::
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2:30-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:30-6:00) ከታች በተራ ቁጥር-5 እና 6 በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎች ወይም ንብረቶችን ዝርዝር የያዘው መደበኛ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት፤ የመወዳደሪያው ሰነድ የሚገባበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ:- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ወደ አየር ጤና በሚወስደው ቶታል ሶስት ማዞርያ ወደ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት የፌደራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ነው:: ስልክ ቁጥር 09-63-442-882 እና 09-13-544-731 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ!
  6. ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው ቦታ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር-1እና3 ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው::
  7. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30(ሰላሳ) ቀናት ነው::
  8. ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው:-
    • ሎት-1 ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
    • ሎት-2 ያገለገለ ባለ ክር እና ባለ ሺቦ ጎማዎች ሽያጭ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
    • ሎት-3 የተቆራረጡ ከመነዳሪዎች ሽያጭ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
    • ሎት-4 ያገለገሉ የተሽከርካሪና የማሽነሪ ባትሪዎች ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
    • ሎት-5 ባዶ ያገለገሉ የዘይትና ግሪስ በርሜሎች ሽያጭ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
    • ሎት-6 ያገለገለ/የተቃጠለ ዘይት (በበርሜል) ሽያጭ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
    • ሎት-7 ባዶ የአፈር ማዳበሪያ ከረጢት UREA&NPS ሽያጭ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
    • ሎት-8 የኬሚካል ጀርካን ባለ 1 ሊትር እና ባለ 5 ሊትር ሽያጭ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
    • ሎት-9 የኤሲ ጋዝ ባዶ ሲሊንደር ባለ 45 ቁጥር ሽያጭ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Omo Kuraz No. 1 and 3 Sugar Factories are selling disposable items in 9 lots, including scrap metal, used tyres, batteries, empty oil barrels, used oil, empty fertilizer bags, chemical jerrycans and AC gas cylinders. Open bid.
Save Tender