ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል::
Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)
ያገለገሉ ጀነሬተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ን/ማ/ሱ-05/19
ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል:: በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ 'PERKINS' ፣ 'AKSA' ፣ 'CGM' እና 'LISTER' ብራንድ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ጀነሬተሮችን እንዲሁም RATO' እና 'KAMA' ብራንድ ባለ 5 KVA እና ባለ ባለ 7 KVA ያገለገሉ ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣ ዝርዝራቸዉ፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል::
- ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ጀነሬተሮች የሚገኙት ገላን ከተማ ቱሉ ጉዶ ቀበሌ ኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን ሲሆን፣ ከታች በ9ኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በቅድሚያ ደዉለዉ ቀጠሮ በማስያዝ ማየት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ መወሳድኮ ገቢ. 2ኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ጀነሬተር የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር፣ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ሕዳር 16 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ መወሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንትና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታዉ ሕዳር 16 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ባስገቡበት፣ በ5ኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሰዉ አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸዉን ጀነሬተር/ጀነሬተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል:: ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::
- ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 0918890721 / 0998411523 / 0114437439 / 0116631729 ይደዉሉ::
✨ messages.ai_summary
Berhan Bank is selling used generators as is: 20 KVA PERKINS, AKSA, CGM and LISTER units and RATO and KAMA 5 KVA and 7 KVA units, kept at its warehouse in Gelan town industrial village. Open to any individual or organization.
