የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል::
Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | የመያዣ ንብረቱ መለያ - የሰሌዳ ቁጥር | ሞተር ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የንብረቱ አይነት | የምርት ዘመን | የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት | ምርመራ |
| 1. | ደመላሽ አድማሱ ታምር | ተበዳሪው | 03-AA-A78222 | 2GD-0650328 | AHTBB3CDX01760095 | ቶዮታ ደብል ጋቢና | 2019 | 6,655,928.85 | 07/03/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት | ቀረጥ አልተከፈለም |
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | የመያዣ ንብረቱ መለያ - አድራሻ | የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር/መለያ | የይዞታው ስፋት በካ.ሜ | የይዞታው አይነት/የሚሰጠው አገልግሎት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት |
| 2. | መቅደስ ንዱ ጌትነት | ሲ.ቢ ጋዝ ማምረቻ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር | ባሕር ዳር ከተማ፣ መሸንቲ | ባህአ/0233/11 | 6000 | ለኢንዱስትሪ/ኦክስጅን ማምረቻ የሚውል ሕንፃ እና ይዞታ | 30,602,126.75 | 22/03/2019 ዓ.ም 3:00-4:00 ጠዋት |
| 3. | ዋጋዬ ካሳዬ ሙላት | ወ/ሮ አበዙነሽ አሰፋ ወንድምነህ | አርባምንጭ ከተማ፣ ውሃ ምንጭ ቀበሌ | SN004010402022 | 297.23 | መኖሪያ ቤት | 5,580,113.30 | 22/03/2019 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት |
| 4. | ዋጋዬ ካሳዬ ሙላት | ወ/ሮ አበዙነሽ አሰፋ | አርባ ምንጭ ከተማ ሴቻ ክፍለ ከተማ ሼቻ ቀበሌ | በቀድሞ ሰ/ክ/ቁ 366፣ በአዲሱ SD-10 | 400 | መኖሪያ ቤት | 12,929,784.02 | 22/03/2019 ዓ.ም 5:00-6:00 ጠዋት |
| 5. | አቶ አማን ተኬ ኦላ | ተበዳሪው | ሻሸመኔ ከተማ አዋሾ ወረዳ | OR002032302002 | 1,201.45 | የንግድ ህንፃ | 59,206,493.70 | 22/03/2019 ዓ.ም 8:00-9:00 ከሰዓት |
| 6. | አቶ አማን ተኬ ኦላ | ተበዳሪው | ሻሸመኔ ከተማ አዋሾ ወረዳ | OR002032302002 | 1,201.45 ካ.ሜ | የንግድ ህንፃ | 59,206,493.70 | 22/03/2019 ዓ.ም 9:00-10:00 ከሰዓት |
መመሪያ:-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው::
- ጨረታ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነው::
- የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል::
- ከመኖሪያ ቤት ዉጪ በጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸናፊ የገዛ ሰዉ በሽያጭ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል::
- የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል::
- ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል::
- በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ ያሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- ንብረቶቹን በጨረታ አሸናፊ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ክፍያ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
- ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ: እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ታትሞ በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በወጣው የጨረታ ማስታወቂያ በተራ ቁጥር 10-12 ተብሉ የተገለጹት ንብረቶች አድራሻ ቀበሌ 02 የተባለው ቀበሌ 20 ተብሎ እንዲነበብ እንገልጻለን::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-11 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል::
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
✨ messages.ai_summary
Commercial Bank of Ethiopia auctions a foreclosed Toyota double-cab pickup and properties: an industrial building in Bahir Dar, houses in Arba Minch and commercial buildings in Shashemene.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
