Ethiopian Customs Commission – Mojo Customs Branch Office invites bidders to purchase abandoned and confiscated goods through auction, including electronics, lighting materials, household items, clothing, industrial equipment, steel products, vehicle spar
Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር ሐ-22/2019 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶች ማለትም AC ADAPTOR, HD TV CABLE, TV WALL MOUNT, LED HIGHBAY LIGHT, SKMEI IRON ADULT HAND WATCH, WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER, OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND, LED STRING LIGHTS, RUBBER NAIL FILTER, S/S MANICURE, METAL DECORATIVE & EYE LASH,ADULT FABRIC CAP, SHOPPING BAG & OTHERS, WALL TRANSFORMER,CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEL PIPE, HEALD FRAME, FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWEL, SINGLE,DOUBLE PORT FACE PLATE & OTHER, SCHOOL BAG, FABRIC ADULT CAP & SUPERMARKET SHELF, CHILDRED SPORT SHOES BRAND & LADYSPORT SHOES BRAND,CONNECTING ROD, BLADE FUSE, VIBRATION ANALYSIS OF CENTERFUGAL BLOWER FAN, ELECTRIC CRANE SCALE, HAIR CLIPER, PERFUME & TROUSER,DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER WITHOUT REIFROGIRETOR፣ የስቴሽነሪና ማስታወቂያ እቃዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል::
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ::
N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል። - ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆኑን እናሳውቃለን::
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል:: ተጫራቾች በወረቀት የሚያስይዙ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ጀምሮ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል::
- የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት:: በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
- በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል:: ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል::
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል::
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-5511/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ወይም 022-236-01-90 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
