Tender Detail

Tender Details

  • Company Cooperative Bank of Oromia (COOP) (የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ)
  • Address Bole Sub-city, Woreda 02, Africa Avenue, Rwanda Embassy Area, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0115 576174
  • Websitehttps://coopbankoromia.com.et/
  • Deadline18 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት እለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተዉና ይዘዉ ሐራጁ በሚካሄድበትና ንብረት በሚገኝበት አድራሻ ቀርበዉ በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ::
  • opening dateሕዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ3:00-5:00 ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል::
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ – ያልተከፈለ የብድር ዕዳን ለማስመለስ የተያዙ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ የሽያጭ ማስታወቂያ።

Cooperative Bank of Oromia (COOP) (የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ)


ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች ስሙ ለተገለፀ ተበዳሪ ያበደረው የብድር ገንዘብ በብድር ውሉ መሠረት ስላልተከፈለ ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መክፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል ያስመዘገበውንና ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ብድር እዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል:: ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ሰዓት እና አድራሻ (ቦታ) በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል::

ተቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምየተሽከርካሪ ዓይነትአበዳሪው ቅርንጫፍየሰሌዳ ቁጥርየሻንሲ ቁጥርየሞተር ቁጥርየጨረታመነሻ ዋጋ ብርጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ
1ወ/ሮ እየሩሳሌም አስፋው መኩሪያወ/ሮ እየሩሳሌም አስፋው መኩሪያደርብ ተግባር ተዮታወረ ጉአአ-03-B20238MROHB8CD2L6116162GD-480387210,000,000ሕዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ3:00-5:00 ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል::
2ኮርነር ስቶን ፋርም ሃ/የተ/የግ/ማህበርመስካም ኢንትግሬትድ ፋርምስ ሃ/የተ/የግ/ማህልዩ ተንቀሳቃሽ (ማቀዝቀዣ ያለው)ሳሪስአ.አ-03-A34257LZZ5BBFH2RE536680YC4E160-33*E3717R102697,000,000ሕዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት ከ8:00-10:00 ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ይካሄዳል::
የተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምየንብረት ዓይነትአበዳሪው ቅርንጫፍጨረታ የቀረበው ንብረት አድራሻ - ክልልክ/ከ ከተማወረዳየቤት ቁጥርየካርታ ቁጥርየቦታው ስፋት በካሬ ሜትርየጨረታ መነሻ ዋጋ ብርጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት
ወ/ሮ እየሩሳሌም አስፋው መኩሪያወ/ሮ እየሩሳሌም አስፋው መኩሪያመኖሪያ ቤትወረ ጉአዲስ አበባቦሌ03-ቦሌ4/18/11/77/9854/00297 ካ.ሜ44,915,816.17ሕዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከ4:00-6:00 ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል::

ተጫራቾች እንዲያውቁት

  1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት እለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተዉና ይዘዉ ሐራጁ በሚካሄድበትና ንብረት በሚገኝበት አድራሻ ቀርበዉ በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ:: ጨረታውን በድርጅት ስም የሚወዳደሩ ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፍቃድ፣ የታደሰ መተዳደሪያ የድርጅቱን ውክልና ማቅረብ አለበት::
  2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓት በተገለፀው መሠረት ባለእዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል:: ባለእዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
  3. ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 0920-506976 ወይም 0917-366842 ወይም 0917-663940 በመደወል መረጃ ማግኘትና መጎብኘት ይችላሉ::
  4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
  5. የጨረታው አሸናፊ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የታክስ ዓይነት ግብር ከፍሎ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ የሚያዞር ይሆናል:: በተጨማሪም ተሽከርካሪዎቹ የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢ የሚከፍል መሆኑን እንገልፃለን::
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Cooperative Bank of Oromia auctions two foreclosed vehicles (a dual-purpose Toyota and a special refrigerated vehicle) and a 297 sq m residential house in Bole Woreda 03, Addis Ababa.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender