Tender Detail

Tender Details

  • Company DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)
  • Address ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5-18-03-56
  • Websitehttps://dashenbanksc.com/
  • Deadline03 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceFree
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 25% (CPO በዳሸን ባንክ አ.ማ ስም)
  • opening date24/03/2019 ዓ.ም ከ4:00-6:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

ዳሸን ባንክ አ.ማ በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ የወጣ)

DASHEN BANK S.C (ዳሽን ባንክ አ.ማ)


በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር ዳባ/ብማ/0042/26

ዳሸን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚከተለውን የተበዳሪ/አስያዥ መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል።

ተ.ቁየተበዳሪው ስምአበዳሪው ቅርንጫፍየአስያዥ ስምከተማክ/ከተማየካርታ ቁጥርየቦታ ስፋትየንብረት አይነትየጨረታ መነሻ ዋጋቀንሰዓትቦታ
1[የተበዳሪ ስም][ቅርንጫፍ]ወ/ሮ [የአስያዥ ስም]አዲስ አበባለሚ ኩራለኩ-ፋ-9/29/5/37113/0487/5/01175 ካ.ሜየመኖሪያ ቤት39,825,57024/03/20194:00-6:00መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት አድራሻ

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በዳሸን ባንክ አ.ማ. ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
  2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል።
  3. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ ታክስ፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው /አሸናፊው/ ይከፍላል።
  4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  5. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
  6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
  7. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠናቀቀ ሊራዘም ይችላል።
  8. ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ከባንኩ ሲደርሰው ብቻ ነው።
  9. በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፊ/ ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል። ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቅድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሀራጅ ደንብ የተቀመጡ ግዴታቸውን አያስቀርላቸውም።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0111-70-45-49 ወይም 0111-70-40-38 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

ዳሸን ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Dashen Bank S.C is re-auctioning a mortgaged residential house on a 175 sq m plot in Lemi Kura Sub-city, Addis Ababa, sold as is under its foreclosure powers. Public auction held at the property; the bank may offer partial loans to eligible winners.
Save Tender