Tender Detail

Tender Details

  • Company Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
  • Address HQ Building, The Gambia st, Legehar, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0115 15 07 11
  • Websitehttps://www.bankofabyssinia.com/
  • Deadline01 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • opening dateሕዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው አሸናፊ የጨረታ ከፍተኛ ዋጋ አቀራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የጨረታው ቦታ ሐዋሳ ከተማ ባህል አደባባይ ክ/ከተማ አዳሬ ቀበሌ ዉስጥ በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ሐዋሳ ዲስትሪክት ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ባለዉ የሕግ ክፍል ዉስጥ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁየተበዳሪው ስምየመያዣ ሰጪው ስምየንብረቱ አይነት እና አገልግሎትየቦታው ስፋት በካ.ሜየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥርንብረቱ የሚገኝበት አድራሻየጨረታው መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚካሄድበት ቀንየምዝገባ ሰዓትየጨረታ ሰዓትጨረታው የወጣዉ
1አቶ አለሙ አመኑተበዳሪዉየመኖሪያ ቤት463.752081አለታ ወንዶ ከተማ1,117,169.13ሕዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም4:30-5:305:30-6:00ድጋሚ
2አቶ አለሙ አመኑአቶ አለማየሁ አለሙየንግድ ቤት2652082አለታ ወንዶ ከተማ2,557,684.39ሕዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም8:30-9:309:30-10:00ድጋሚ
3አቶ አለሙ አመኑተበዳሪዉየመኖሪያ ቤት512.552283አለታ ወንዶ ከተማ1,040,408.24ሕዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም4:30-5:305:30-6:00ድጋሚ
4አቶ አለሙ አመኑአቶ አለማየሁ አለሙየመኖሪያ ቤት645.092060አለታ ወንዶ ከተማ2,850,326.87ሕዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም8:30-9:309:30-10:00ድጋሚ
5አቶ አለሙ አመኑተበዳሪዉየንግድ ቤት799.18የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር SD001080402006ሐዋሳ ከተማ13,530,735.32ሕዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም4:30-5:305:30-6:00ድጋሚ
6አቶ አለሙ አመኑተበዳሪዉበካርታው ለመኖሪያ ቤት የተፈቀደ እና በግንባታ ላይ የሚገኝ1277.92የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር SD001080402002ሐዋሳ ከተማ44,549,306.66ሕዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም8:30-9:309:30-10:00ድጋሚ
7አቶ አለሙ አመኑተበዳሪዉየንግድ ቤት700የቦታ ልዩ መለያ ቁጥር HUB114/98CB-5ሐዋሳ ከተማ16,569,858.94ሕዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም4:30-5:305:30-6:00ድጋሚ
✨ messages.ai_summary
Bank of Abyssinia auctions seven foreclosed properties of one borrower: residential and commercial houses in Aleta Wondo town, and commercial houses plus a residential building under construction in Hawassa town.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender