የግበ ዲዴሳ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን የአፈር ማዳበሪያ (DAP እና UREA) ማጓጓዣ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
በምዕራብ ኦሮሚያ የግበ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን
ለ2019/2020 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው ግበ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ለ2019/2020 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያን ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ መጠን እና ዓይነት፡-
- DAP /ዳፕ) 244,663.00 ኩንታል
- UREA (ዩ ሪ ያ ):- 326,810.00 ኩንታል
- ጠቅላላ ድምር፡- 571,473.00 ኩንታል
ሲሆን የአፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበት ቦታ ከተለያዩ የዩኒዬን መጋዘኖች እስከ መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ወይም ማህበራት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብረ 700.00 በመክፈል ምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ በሚገኘው ግበ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን መግዛት ይቻላል።
በዚህ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሆኖ በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል። የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚቀጥለው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ (በዓል) ከሆነ በሚቀጥሎ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ በሚገኘው ግበ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ይከፈታል።
ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ወይም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሞባይል 09 75-50-50-59 ወይም በስልክ ቁጥር 0576617841
