የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር መደበኛ 02/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ /እስቴሽነሪ እና የትራንስፖርት/መጓጓዣ/ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው
- ከታክስ ባለስልጣን /ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ግዥ ከ500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሳሪያ ግዥ 42,000/አርባ ሁለት ሺህ /ብር እና ለትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር እና ከዛ በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መ/ሂ/ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መ/ሂ/ ማስያዝ የሚችል ።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል ወይም በገንዘብ ጽ/ቤት ብቻ ይሆናል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500/ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።
- የጨረታ ሳጥኑን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ /ካላደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊው በየዳ ወረዳ ድል-ይብዛ ከተማ በአምስቱ ንብረት መጋዝን ማቅረብ የሚችል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል እና ጠቅላላ ዋጋ እና ጠቅላላ ድምር ያላስቀመጠ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0918352228 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Beyeda Woreda Finance Office (North Gondar Zone, Amhara) seeks suppliers of stationery and transport services for the woreda offices, with delivery to its store in Dil-Yibza town. Open to traders with a renewed licence, TIN, registration certificate and tax clearance.
