የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመኪና መለዋወጫ፣ የህክምና፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽሕፈት መሳሪያና የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
የተለያዩ አይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር (ሁለት) 02/ 2019 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎች፡ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፅ/መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች [...] በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምሥክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርቲፍኬት ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ
- የተሞላው ዋጋ ከብር 50,001.00 እስከ 500,000.00 ከሆነ የብር 5,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተሞላው ዋጋ ከብር 500,001.00 እስከ 1,000,000.00 ከሆነ የብር 10,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተሞላው ዋጋ ከብር 1,000,001.00 እስከ 5,000,000.00 ከሆነ የብር 50,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተሞላው ዋጋ ከብር 5,000,001.00 በላይ ከሆነ የብር 200,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ CPO/ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የቴክኒካል ስፔስፊኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር መብት አለው።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 0910062954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Region Police Commission seeks suppliers of various items for its operations, including vehicle spare parts, medical supplies, electronics, stationery and cleaning supplies. Open to licensed, VAT-registered suppliers with a supplier certificate. Open bid.
