የአጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የቢሮና የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት እና ልዩ ልዩ እቃዎች ግዥ
የአፄ ቴዎድሮስ የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የአጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች ፣ ልዩ ልዩ እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
| የሎት.ቁ | የሎት ዝርዝር | CPO |
| ሎት1 | የደንብ ልብስ | 32,000.00 |
| ሎት2 | አላቂ የቢሮ እቃዎች | 4,000.00 |
| ሎት3 | አላቂ የትምህርት እቃዎች | 16,000.00 |
| ሎት4 | አላቂ የፅዳት እቃዎች | 5,713.71 |
| ሎት5 | ልዩ ልዩ እቃዎች | 1,600.00 |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ፡-
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቹ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው መሆን አለበት።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊትለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ ነው።
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰአት 2፡30 እስከ 11፡00 ሰአት በት/ቤቱ የፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማፃፍ እና ለሚያመርቱት ምርት (እቃ) እንደማንኛውም ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት በመጨረሻው ቦታ ላይ ስም፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 የአንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰአት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ወይም ዕረፍት የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ዋስትና ማሲያዝ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ባሸነፉበት የእቃዎች ብዛት ላይ መስሪያ ቤቱ 20% መጨመርም 20% መቀነስም ይችላል። እንዲሁም መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አቃቂ ንግድ ባንክ በስተጀርባ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-471-59-63
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የአጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Atse Tewodros Primary School (Akaki Kaliti Sub-city, Woreda 03) seeks suppliers in five lots: uniforms, office supplies, educational materials, cleaning supplies and miscellaneous items. Open to licensed, VAT-registered suppliers with a supplier certificate. Open bid.
