የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ ህትመት፣ ጽዳት እና የተለያዩ የሙያ ማሰልጠኛ ግብዓቶች ግዥ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ሎት | የግዥው አይነት ዝርዝር | የጨረታ ማስከበሪያ CPO |
| 1 | የደንብ ልብስና የስፖርት ማሰልጠኛ ግብዓት | 40,000.00 |
| 2 | የጽሕፈት መሣሪያዎች | 30,000.00 |
| 3 | ህትመት | 15,000.00 |
| 4 | አላቂ የፅዳት ዕቃዎች | 40,000.00 |
| 5 | የስራ ልብስ ስፌት | 10,000.00 |
| 6 | የኤሌክትሮኒክስና ቪዲዮግራፊ ማሰልጠኛ ግብዓት | 50,000.00 |
| 7 | የፎቶ ኮፒ እና ፕሪንተር ቀለሞች | 30,000.00 |
| 8 | የአይሲቲ ማሰልጠኛ ግብዓት | 50,000.00 |
| 9 | የከተማ ግብርና ማሰልጠኛ ግብዓት | 30,000.00 |
| 10 | የአውቶሞቲቭ ማሰልጠኛ ግብዓት | 50,000.00 |
| 11 | የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ግብዓት | 30,000.00 |
| 12 | የቴክስታይል ጋርመንትና ሌዘር ማሰልጠኛ ግብዓት | 40,000.00 |
| 13 | የኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ ግብአት | 40,000.00 |
| 14 | የብረታብረት ማሰልጠኛ ግብዓት | 40,000.00 |
| 15 | የእንጨት ሥራ ማሰልጠኛ ግብዓት | 40,000.00 |
| 16 | የእስቴቲክስ ማሰልጠኛ ግብዓት | 50,000.00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበትን፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎችና በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ/ዌብሳይት/ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢ/ያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል፤
- ከብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ፣ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ለጨረታ ሰነዱ መግዣ ለእያንዳንዱ /ሎት/ የግዥ አይነት / የተቀመጠውን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በኮሌጁ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000010827632 በመክፈል ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመ/ግዢ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 012 መውሰድ ይቻላል።
- ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት ፅሁፍ በማድረግ በአንድ ትልቅ ካኪ ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ፣ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ከቋቋማቸው አካል የተሰጠ የዋስትና ደብዳቤ ኦርጅናል በታሸገው ፖስታ ውስጥ መካተት አለበት። በኦርጅናልና በቅጅው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናል የባላይነት ይኖረዋል።
- በመጫረቻ ሰነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል። ግምገማው ከ60 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ ኮሌጁ እንደ አስፈላጊነቱ ግምገማው እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ተጫራቾች ያቀረቡትን የመጫረቻ ዋጋ እንዲያራዝሙ የመጠየቅ መብት ያለው ሆኖ ለማራዘም ፈቃደኛ ያልሆነ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል።
- የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል። ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታዎቹ በተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ መጫረት አይችልም።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና እስከ ጨረታ መክፈቻ ሰዓት ድረስ እንዲቀርቡ በተጠየቀባቸው ናሙናቸውን በኮሌጁ ናሙና ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ስዓትን አያስተጓጉልም።
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቅሬታ መስሚያ ቀናት ቅሬታ ካሎት በጽ/ቤቱ ማቅረብ ይቻላል። እንዲሁም ከ5 የቅሬታው መስሚያ ቀናት በኋላ ባሉ 5 የስራ ቀናት ውል መውሰድ የሚችል።
ማስታወሻ
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱ አንድ አካል ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የሰፈሩት ዝርዝር መረጃዎች፣ በተጫራቾች መመሪያ እና ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በትኩረት ማንበብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ላይ ቫትን ካላካተቱ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል።
በምግብና በመጠጥ አቅርቦት ላይ ለሚወዳደሩ ነጋዴዎች ኮሌጁ በየአንድ ወር የገበያ ጥናት በማካሄድ የዋጋ ጭማሪ እና ቅነሳ በማድረግ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል የሚፈፀም ይሆናል።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 6ኪሎ ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ።
ተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ፡- 0118 28 29 52
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Teferi Mekonnen Polytechnic College (Addis Ababa) seeks suppliers in 16 lots: uniforms and sports items, stationery, printing, cleaning items, tailoring, toner, and training inputs for ICT, electronics, automotive, construction, metal, wood, textile, hotel, agriculture and aesthetics.
