የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የጽሕፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ እና የዶዘር ኪራይ
የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት፡-
1. የጽሕፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ 2. የደንብ ልብስ 3. የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች እና የዶዘር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሳሪያ የሚወዳደሩ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዲራሼ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው። የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው 15ኛው ቀን የዕረፍት/የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል። ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 14 በ15ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
- ተወዳዳሪዎች ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሠረት ናሙና የማቅረብና አሸናፊዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ 10% ለሦስት ወር የሚቆይ ዋስትና የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው። ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
- አሸናፊዎች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ ጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተወዳዳሪዎች የሚሞሉት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ90 ቀናት በታች መሆን እንደሌለበት እናሳስባለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0467740344/343 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
የጋርዱላ ዞን ዲ/ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Dirashe Woreda Finance and Plan Office (Gardula Zone, South Ethiopia) seeks suppliers of stationery and office supplies, uniforms, and veterinary medicines and equipment, plus dozer machine rental. Open to licensed, VAT-registered suppliers; veterinary bidders need a competence certificate.
