የዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቁራቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Zemen Insurance S.C (ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ)
ዘመን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር (006/2019)
የዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቁራቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን የተሽከርካሪ ቁራጭ እንዲሁም ሌሎች ቁራጮችን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በሌ ጋይሌ እና ዓለም ህንጻ ሁለተኛ ወለል ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የሚመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸዋ ዳቦ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ (RICOVERY) ውስጥ በማየት ከመስከረም 24 ቀን 2019ዓ/ም እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 2.00 ሰዓት እስከ 6.00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት 7.00 ሠዓት እስከ 11.00 ሠዓት ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ቁራጭ ንብረቶችንና ተሽከርካሪዎቹን ከመስከረም 24 ቀን 2019ዓ/ም እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 07 ቀን 2019ዓ/ም ከጠዋቱ 4.00 ሠዓት ተዘግቶ በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 07 ቀን 2019ዓ/ም ከጠዋቱ 4.30 ሠዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር ፐርሰንት) ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ ወይም(ZEMEN INSURANCE S.C) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከቀረጥ ነጻ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱት ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ለሚነሱት ማንኛውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) 15 % (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ፡፡
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካላነሱ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎችንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጥሉ በአንድ ጊዜ ክፍያው በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን ከሪከቨሪ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ለማስፈጸም የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ማንኛውም ጉዳይ (ችግር) ኩባንያው ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ፡- 09-44-17-36-73 ወይም 09-11-47-30-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዘመን ኢንሹራንስ አ/ማ
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
Zemen Insurance invites bids for the sale of vehicle parts and other items from vehicles it has compensated and taken over, sold as-is. Bidders must buy the tender document, deposit 10% of the starting price via CPO, and submit prices before VAT.
