ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት የተለያየ እቃ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት በኅትመት የተበላሸ ጋዜጣ፣ ፕሬስ ላይን በርሜል፣ ትልቅ እና ትንሽ የቀለም ቆርቆሮ፣ አገልግሎት የሰጡ ሃዩንዳይ እና ቶዮታ አወቶሞቢል መኪኖች፣ አገልግሎት የሰጡ ጐማዎች፣ የተቃጠለ ዘይት፣ አ/ት የሰጡ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣ አሸንዳ፣ በአ/ት የሰጠ ቶነር፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የፎርክሊፍት ጐማዎች፣ ጐልድ ፎይል፣ የቀለም ባልዲ፣ አ/ት የሰጠ ከምፒውተርና ፕሪንተር ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ድረስ በዋናው ቅጥር ግቢ በሚገኘው የማርኬቲንግ ሽያጭ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛትና ንብረቶቹንም ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዛበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፣ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት
