Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
  • Address , Phone: 011 896 5521
  • Website
  • Deadline28 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/
  • opening dateSep 28, 2026 10:15 AM
  • Categories Disposal Sale , Used Items

ያገለገሉ ጎማዎች ስክረፕ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ጎማዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ያገለገሉ ጎማዎች ስክረፕ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ጎማዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ደርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.     በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሰነድ ለመግዛትሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖረባቸዋል።

2.     ተጫራቾች የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 2 ፎቅ የግዢ ንብረት ፋስሊቲ ዳይሩክቶሬት ቢሮ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዙ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፁት ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4.     ጨረታው 18/1/2019 ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥ ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቾች በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

5.     በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስረከቢያ ... (CPO) ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ያደርጋል።

6.     ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጨራች ከተገኘ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

7.     አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ያገለገሉ ጎማዎችና ስክረፕ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

8.     ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 896 5521 ወይም 011 896 5522 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

9.     ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

ቦብማርሌ አደባባይ አጠገብ ገርጂ መታጠፊ

የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 08/09

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

Save Tender