የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሣሪስ ሚችልኮትስ በሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን 57 ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎችን፤ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሣሪስ ሚችልኮትስ በሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን 57 ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎችን፤ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ/ ብር በመከፈል ከጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እንዲሁም ከሠዓት በኋላ 7፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋ/መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው፡፡
- ጨረታው መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የስም ማዘዋወሪያና ተያያዥ ክፍያዎች በአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የመረከቢያ ሰነድ ወይም የሽያጭ ትዕዛዝ ደብዳቤ የሚሰጠው በጨረታ ላሸነፈበት መጠን በቅድሚያ ክፍያ ሲፈፅም ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት በመከፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ከ5ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡
- አሸናፊው በራሱ ወጪ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማስጫንና ማጓጓዝ አለበት፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
