በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 18/2019 ፣ 19/2019፣20/2019፣21/2019፣22/2019፣23/2019፣24/2019፣25/2019፣26/2019 እና 27/2019 የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 18/2019 ፣ 19/2019፣20/2019፣21/2019፣22/2019፣23/2019፣24/2019፣25/2019፣26/2019 እና 27/2019 የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዚያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስና የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፤ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ጊርቦከስ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 18/2019 በቀን 02/13/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 19/2019 በቀን 05/13/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 20/2019 በቀን 04/01/2019 ዓ ም፣ ጨረታ ቁጥር 21/2019 በቀን 07/01/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 22/2019 በቀን 11/01/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 23/2019 በቀን 14/01/2019 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 24/2019 በቀን 18/01/2019 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 25/2019 በቀን 21/01/2019 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 26/2019 በቀን 25/01/2019 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 27/2019 በቀን 28/01/2019 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡
በመሆኑም
- በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 - 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክመጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና( CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም፣ ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም፣ መስከረም 04/2019 ዓ.ም፣ መስከረም 07/2019 ዓ.ም፣ መስከረም 11/2019 ዓ/ም፣ መስከረም 14/2019 ዓ/ም፤ መስከረም 18/2019 ዓ.ም፣ መስከረም 21/2019 ዓ.ም፣ መስከረም 25/2019 ዓ.ም መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) እና ከላይ በተቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በዐ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ.ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
በተራ ቁጥር 01- 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019 በቀን 4/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 11/2019 በቀን 7/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 12/2019 በቀን 11/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 13/2019 በቀን 14/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 14/2019 በቀን 18/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 15/2019 በቀን 21/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 16/2019 በቀን 25/02/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 17/2019 በቀን 28/18/2018 ዓ.ም ጨረታ ከጠዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፤ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) APHC CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት፣ ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከአክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የኦከሽን ኢትዮጵያ ኢማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251905115511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 45 37 እና 011 668 41 93 ደውሎ ይጠይቁ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
