የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የምንጠቀምበት 10% ፈላሽ ሶዲየም ሃይፖከሎራይት (Sodium Hypochlorite) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ፈጽሞ ለመግዛት ይፈልጋል፤ እንዲሁም የእቃውን ጥራትና የአቅርቦቱ ብቃት ታይቶ ለተጨማሪ ለአንድ ዓመት የሚራዘም ይሆናል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የምንጠቀምበት 10% ፈላሽ ሶዲየም ሃይፖከሎራይት (Sodium Hypochlorite) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ፈጽሞ ለመግዛት ይፈልጋል፤ እንዲሁም የእቃውን ጥራትና የአቅርቦቱ ብቃት ታይቶ ለተጨማሪ ለአንድ ዓመት የሚራዘም ይሆናል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ያላቸው፡፡
- ቫትና ቲን ቁጥር የተመዘገቡ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ብር 80,000.00 /ሰማንያ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ከዋናው ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው።
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በስፔስፊኬሽኑ መሠረት ተመላሽ በሚሆን ታንከር ወይም ጀሪካን በማሸግ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ድረስ በየወሩ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው በአንድ አመቱ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ መስጠት የሚችል፡፡
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ድሬዳዋ ስልክ ቁጥር 0251124892 ፓ.ሣ.ቁ 446
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
አ
