Tender Detail

Tender Details

  • Company የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሱ የወረዳ 10 አስተዳደር ህንፃ ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline14 Sep 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200/ሁለት መቶ ብር/
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 10 ቀን ቆይቶ በ 11 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Other , Services , Others

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት አግልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት አግልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መረጃ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Tin) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ያላቸው፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ CPO በባንክ የተረጋገጠ በየሎቱ ሎት-1 የፅህፈት መሳርያ 40,000፣ ሎት-2 የደንብ ልብስ 40,000፣ ሎት-3 የጽዳት እቃዎች 35,000፣ ሎት-4 የህትመት ስራዎች 5,000፣ ሎት-5 የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ 1,000 ሎት-6 የእንስሳት ህክምና አላቂ እቃዎችና መድሃኒቶች 1,000፣ ሎት-7 ትራንስፖርት አገልግሎት 5,000፣ ሎት-8 ለቢሮ መስተንግዶ 2,000፣ ሎት-9 እንጨት ነክ እድሳትና ጥገና 1,000 ሎት-10 የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች ግዥ 30,000 ሎት 11 የልብስ ስፌት 1,000 ሎት 12 የጭነት /የጉልበት/ አገልግሎት ከተደራጁበት መ/ቤት ደብዳቤ በማፃፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ/ከተማ የወረዳ 10 ለፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች/ሎቶች ላይ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙናው መግባት ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ዋጋውን ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

* ለተጨማሪ መረጃ፡- ን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሎ የወረዳ 10 አስተዳደር ህንፃ ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender