Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋሞ ዞን የጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0913868795
  • Website
  • Deadline13 Sep 2026, 5:06 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300 (ሶስት መቶ) ብር
  • opening dateየጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Categories Office Supplies And Services , Vehicle (Garage Service) , Vehicle Spare Parts

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አግልግሎት የሚውል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አግልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 ጽ/መሣረያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ እና
  • ሎት 3 የመኪና ጥገና አግልግሎት ግዥ

በውል የምታሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል። በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦

  1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  3. የዘመኑን የግብር ክፍያ ማረጋገጫ እና TIN ያላቸው።
  4. የቫት/ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
  5. በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ያሸነፈበትን ዕቃ ዝርዝር በተፈለገበት ጊዜና ሰዓት በራሳቸው ወጪ እስከ ጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ንብረት መጋዘን ማቅረብ የሚችሉ፤ የመኪና ጥገና በራሱ ጋራዥ መጠገን የሚችል።
  7. አገልግሎት የማይሰጡና የጥራት ችግር ያለባቸውን ዕቃዎች መመለስና መተካት የሚችሉ።
  8. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በመቀረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚከፈተው 16ኛው የሥራ ቀን ሲሆን፤ ሎት-1, 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡10 ላይ የሚከፈት ሲሆን ሎት-2, 4፡30 ታሽጎ 4፡40 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ሎት-3 ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡10 የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ላይ ባይገኙ ጨረታውን አያስተጓጉልም።
  10. ተጫራች በእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /አምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በተመሳሳይ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የብድ ቦንድ/ የባንክ የክፍያ ማዘዣ ማቅረብ ይኖርበታል።
  11. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባቸው፤ ካልተገሰጸ ግን ቫትን ያካተተ ተብሎ ይወሰዳል።
  12. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በዕቃዎች እያንዳንዱን ዕቃ በዕቃው ዋጋ በማቅረብ ይሆናል።
  14. ክፍያ የሚፈጸመው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ድረስ አቅርቦ የዕቃዎቹ ደረጃ ከተረጋገጠ በሞደል 19 ገቢ ከተደረገ በኋላ ብቻ ይሆናል።
  15. መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ 0913868795 /0954774308

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋሞ ዞን የጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

Save Tender