በአቃ/ቃ/ከ/ከ የወረዳ 10 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስታወቂያ ቁጥር ፋ/ጽ 002/2019
በአቃ/ቃ/ከ/ከ የወረዳ 10 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የደንብ ልብስ
- አላቂ ቢሮ ዕቃዎች
- ህትመት
- የፅዳት ዕቃዎች
- ሌሎች አለቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የጓሮ አትክልት
- ጥገና(የቢሮ ኤልክትሮኒክስ)
ሎት1፤ CPO 100,000/ አንድ መቶ ሺህ/ ብር፡
ሎት2፤ CPO 40,000/አርባ ሺህ/ ብር፤
ሎት3፤ CPO 100,000/ አንድ መቶ ሺህ/ ብር
ሎት 4፤ CPO 30,000/ ሰላሳ ሺህ/ ብር
ሎት5፤ 50,000/ሃምሳ ሺህ/
ሎት6 CPO 12,000(አስራ ሁለት ሺህ)
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- በስራው ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢነት ተመስጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከላይ በየሎቱ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር በምል CPO ማሰራት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድን የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነድ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋት 2፡30 እሰከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚሰሩ ከስራና ክህሎት ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ በማምጣት በተፈቀደላቸው የስራ ዘርፍ/የሚያመርቱት ምርት/ላይ ብቻ ያለክፍያ የጨረታ ሰነድ መውሰድና የጨረታ ማስከበሪያ ሳያስዙ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ከሚያመርቱት ምርት ውጭ ከሆኑ ዕቃዎች ላይ እንደማንኛውም ነጋዴ የጨረታ ሰነድ መግዛትና CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የእቃ ናሙና ከየአይነቱ አንዳንድ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ የጨረታ ተወዳዳሪ ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ በ5 ቀን ውስጥ ከግዥው ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
- አቅራቢው ተጫራች በውሉ መሰረት ግዴታውን ካልተወጣ ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት 10% ገንዘብና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO ሙሉ በሙሉ የሚወረስ ይሆናል።
- ተወዳዳሪ ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ሆኖ መቅረብ አለበት።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡
- በአ/ቃ/ ክ/ከ የወ/10 ፋ/ጽ/ቤት ወደ ጎሮ መሄጃ ቀርሳ አደባባይ ከአስፓልት በስተቀኝ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0961 091 86 / 0909 289 281 / 0921 067 960
በአቃ/ቃ/ክ/ከ የወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
