በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለጹት መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡-
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡02/2019
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለጹት መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡-
- ሎት 01. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 02. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 03. የህትመት አገልግሎት
- ሎት 04. የደንብ ልብስ
- ሎት 05. የድንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 06. ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት 07. ኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 08. የኤልክትሮኒክስ እና ጀኔሬተር ሰርቪስና ጥገና አገልግሎት
- ሎት 09. መድሀኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት
- ሎት 10. የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች/Medical Equipment/
- ሎት 11. የህንፃ ጥገና እና ማስፋፊያ ስራ
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢያዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን/TIN/፣ የቫት/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 10,500(አስር ሺህ አምስት መቶ) ፣ሎት2. 13,500(አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት3. 6800(ስድስት ሺህ ስምንት መቶ) ፣ ሎት4. 10,000(አስር ሺህ) ፣ ሎት5. 6000(ስድስት ሺህ) ፣ ሎት6. 36,500(ሰላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት7. 20,700(ሃያ ሺህ ሰባት መቶ) ፣ ሎት8. 4,500(አራት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት9. 25,000(ሃያ አምስት ሺህ)፣ ሎት10. 30,000(ሰላሳ ሺህ) እና ሎት11. 30,000(ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል አብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ የግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቪሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ የግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት በአብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 2ኛ ፎቅ አደራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01፣ ለሎት 02፣ ሎት 04፣ ሎት 05፣ ሎት 06፣ እና ሎት 07 በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣ ሎት 03፣ ሎት 08፣ ሎት 09፣ ሎት 10 እና ሎት 11 በመ/ቤቱ የፍላጎት መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ለእያንዳንዱ እቃዎች ነጠላ ዋጋ ከቫት ጋር እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፓርት ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ በስልክ ቁጥር፡- 011-273 4349 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡
- ልደታ ክ/ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ
