በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮ ፣ የደንብ ልብስ፣ ለስልጠና፣ የተለያዩ ምግብ አይነቶች እና ለምርት ስራ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮ ፣ የደንብ ልብስ፣ ለስልጠና፣ የተለያዩ ምግብ አይነቶች እና ለምርት ስራ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-
1. ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
2. ከላይ ለተጠቀሰው እቃ የማወዳደሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፕ.ኦ ብቻ በ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. አሸነፊው የሚያቀርበው እቃ መስፈርቱን የማያሟላ ሆኖ ከተገኘ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት።
4. የሚቀርቡት ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
5. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በመግዛት ከጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾ የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. አሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የዕቃውን ሙሉ ዋጋ 10% ኮንትራት አማውንት (በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ዕቃውን የማጓጓዣ መጫኛና ማውረጃ ወጪውን በመቻል ጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
10. የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው በጥያቄው መሰረት መቅረቡ እና ንብረት ክፍል ገቢ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፤
11. ተጫራቾች በቀረበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ 5 (አምስት) ቀን ውስጥ በመስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
እቃ ለማቅረብ የሚትወዳደሩ በሙሉ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስልክ ቁጥር 0920 379 891 ወይም 0913 181 413 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
