Tender Detail

Tender Details

  • Company የአሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ
  • Address , Phone: 0924974707/0911106356
  • Website
  • Deadline21 Sep 2026, 5:08 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200 የማይመለስ
  • opening dateበ15ኛው ተከታታይ ቀን ልክ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks , Firewood

አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ ኮሌጅ 2019 ዓ/ም ለመደበኛ እና አጫጭር ስልጠና አሰልጣኞች የቀለብ አገልግሎት የሚውል


የጨረታ ማስታወቂያ

አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ ኮሌጅ 2019 ዓ/ም ለመደበኛ እና አጫጭር ስልጠና አሰልጣኞች የቀለብ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የእህል እና ጥራጥሬ ፣
  • ሎት 2 ምግብ ማጣፈጫ (ባልትና ውጤቶች)፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣
  • ሎት 3 ማገዶ እንጨት

አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች በዚህ ንግድ ሥራ ዘርፍ በመስራት የሚያስችላችሁ ህጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የዘመኑ የ2018/2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (VAT) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በግልጽ የመወዳደሪያ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት ሠነዶቻችውን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 8፡00 ድረስ በዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ድረስ በማምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  5. የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ የሚሞላው ኮሌጁ በሰጠው እስፔሲፊኬሽን ዝርዝር ላይ ብቻ ይሆናል።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ልክ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜ እሁድ /በዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም፣
  8. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፣
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 200 የማይመለስ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ለተከታታይ 15ኛው ቀን አሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፣
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት ከታወቀ ባንክ ጋራንቲ ወይንም ሲፒኦ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል። 2 ፐርሰንት ሲፒኦ ካላቀረበ ወይም ከ2 ፐርሰንት ያነሰ ከሆነ ከውድድሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይሰረዛል፣
  11. ኮሌጁ አሸናፊ ድርጅት የሚመርጠው በእያንዳንዱ ዕቃ ዝቀተኛ ዋጋ እንጂ በጠቅላላው ድምር ዋጋ አይደለም።
  12. አሸናፊዎች የየውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት 10% በማስያዝ ማሸነፉ ከተገለፀላቸው በ5 ቀናት ውስጥ ውል መግባት አለባቸው።
  13. አሸናፊዎች እቃውን የሚያስረከቡት ለሎት 1 ፣ሎት 2 ፣ ሎት 3 በአሶሳ ግት/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ውስጥ ባለው መጋዘን ይሆናል፣
  14. ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ እና ከተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይቻላል።
  15. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
  16. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታ ሂደት አይስተጓጎልም፣
  17. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተሰጠው ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ፌስ ቡክ ገጽ Asosa Agricultural TVET College ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 0924974707/0911106356

የአሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ

Save Tender