በአራዳ ከፍለ ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ልዩ ልዩ እቃ በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገንና ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001
በአራዳ ከፍለ ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ልዩ ልዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የፎቶ ኮፒ ቀለም፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስና የመምህራን ነጭ ጋውን፣ የወንዶችና የሴቶች ቆዳ ጫማ፣ ፕላስቲከ ቡትስ ጫማ፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እስከ እስፒከሩ፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ለት/ቤቱ ልዩ ልዩ ለመስተንግዶ አገልግሎት አቅራቢ፣ ፈርኒቸሮች፣ የጽዳት እቃዎች እንዲሁም የልብስ ስፌት የዕጅ ዋጋ፣ የስፖርት መምህራን የሀገር ውስጥ ሸራ ጫማና ቱታ፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ የጥገና እቃዎች፣ ጥገና የኮምፒውተር፣ የማባዣ ማሽን እና የፕሪንተር ጥገና የሚያስፈልገውን እቃ ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገንና ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው።
- የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ የገዙትን ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ልዩ ልዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የፎቶ ኮፒ ቀለም፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስና የመምህራን ነጭ ጋውን፣ የወንዶችና የሴቶች ቆዳ ጫማ፣ ፕላስቲከ ቡትስ ጫማ፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እስከ እስፒከሩ፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ለት/ቤቱ ልዩ ልዩ ለመስተንግዶ አገልግሎት አቅራቢ፣ ፈርኒቸሮች፣ የጽዳት እቃዎች እንዲሁም የልብስ ስፌት የዕጅ ዋጋ፣ የስፖርት መምህራን የሀገር ውስጥ ሸራ ጫማና ቱታ፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የኮምፒውተር፣ የማባዣ ማሽን እና የፕሪንተር ጥገና የሚያስፈልገውን እቃ ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገንና ለመግዛት ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200,00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዝርዝር ተፅፎ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /ብር 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ በማስያዝ በመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውሰጥ ከጠዋቱ 2፡30-6:30 እና ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች ከአሸነፈ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት።
- ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
- ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ላይ ተንተርሶ ዋጋ መጨመር አይቻልም።
- ያቀረቡበት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ገበያ የሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ካመጡ የሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ መስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም መ/ቤቱ ዕቃዎችንም 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ የምንችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ
ስ/ቁ 0118-68-13-56/57
አድራሻ፦ ግቢ ገብርኤል በስተጀርባ ባዕታ ክሊኒክ አጠገብ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
