Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address , Phone: 0116377277
  • Website
  • Deadline20 Sep 2026, 3:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 15 ቀን ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Water Pipes And Fittings

የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት ከታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 0001/2018

የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት ከታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት- 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት- 3 የቧንቧ መገጣጠሚያ
  • ሎት-4 የኤሌክትሪክ እቃ

በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ፡

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ያለው የግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፓስታ የእንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትከከል በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የድምር ስህተት ካለ በአንድ መስመር በመሰረዝ ፖራፍ በማድረግ የተስተካከለውን በምርመራ አምድ ላይ በትከከል መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ 5፡00 በስራ ሰዓት የተዘጋጀው ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል በደ/ብ/ከ/ው/ፍ/አ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/2 በመቅረብ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  4. ተጫራቾች ቴከኒከ ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው ለብቻው ቴክኒካል ሰነድ በማዘጋጀትና ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በሁለት በተለያዩ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ወደተዘጋጀው ቴከኒካል ሰነድ ጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ በተገለፀው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ድረስ በ3፡29 ሰዓት ከፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 3፡30 ይታሸጋል፣ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት የደ/ብ/ከ/ው/ፍ/አ/ድርጅት በአዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፣ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታው በአራት ሎት ስለተከፈለ የመክፈቻ ሰዓት ሊሻሻል ይችላል የመክፈቻው ቀን በዓል ላይ ከዋለ በማግስቱ ይከፈታል።
  6. የጨረታውን ማስከበሪያ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በማስላት በባንከ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ሆኖም ያስያዘበትን የገንዘብ መቀበያ ሰነድ ኮፒ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  7. እሸናፊው የሚለየው ሎት1 በጥቅል ዋጋ ሎት 2.3.4 በነጠላ ዝቅተኛውን በማወዳደር ሆኖ የተሞላው ዋጋ ከወቅቱ ገበያ ጥናት በላይ ከሆነ ውድቅ ይደረጋል።
  8. አሸናፊው ድርጅት ወዲያውኑ ውል ይፈጽማል የውል ማስከበሪያ በአሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ ብር 10% ያስይዛል።
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም።
  10. ተወዳዳሪዎች እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት ማመልከቻ በመፃፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ።
  11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃ በራሱ ወጪ ደ/ብ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ማድረስ ይጠበቅበታል።
  12. አሸናፊው ድርጅት ድርጅቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሠረት እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።
  13. ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን 25% በመጨመርና በመቀነስ ማሻሻል ይችላል።
  14. ተጫራቾች ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች ሣምፕል ወይም ናሙና እስከ 15ኛው ቀን 11፡29 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  15. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በድርጅቱ ባለሙያ ጥራቱ ተገምግሞ ትከከል ሆኖ ሲረጋገጥ ከፍያ ሚከፈል ይሆናል።
  16. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. የጨረታ ሰነድ ወይም የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ45ቀናት የፀና ይሆናል።
  18. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  19. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  20. ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-637-72-77 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት

Save Tender