Tender Detail

Tender Details

  • Company ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር እንደሄዱ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline18 Sep 2026, 5:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00 ብር (አምስት መቶ ብር ብቻ)
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ 11 ኛው ቀን 04፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በለሚ/ኩ/ከ/ከተማ የወረዳ 9 ጎሮ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውል እቃ ግዥ ሲሆን፡-


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በለሚ/ኩ/ከ/ከተማ የወረዳ 9 ጎሮ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቡድን በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውል እቃ ግዥ ሲሆን፡-

  • ሎት 1 ደንብ ልብስ ፣
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
  • ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
  • ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች ፣
  • ሎት 5. የልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 6. የህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች ፣
  • ሎት 7 ቋሚ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 8. የህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በዚሁ መሰረት:-

  1. ተጫራቾች በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቹ በማንኛውም መንግስት መ/ቤትም ሆነ በግል ድርጅት በጨረታ ምክንያትም ይሁን በሌሎችም ያልታገዱና ያልተከሰሱ መሆን አለበት፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ አስተባባሪ ቢሮ 500.00 ብር (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በመጨረሻ ቀን ልክ 11:00 ሰአት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ልክ 4:30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ዘኛው ቀን ቅዳሜ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሰኞ በተባለው ሰአት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ለመከፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል። ለአንድ እቃ 2 አይነት ናሙና ያቀረበ ተጫራች እንዲሁም በሚቀርበው ናሙና ላይ የተለየ ምልክት ካስቀመጠ የቀረበው ናሙና በሙሉ የሌላውን ተጫራች እድል የሚያሳጣ ስለሆነ ውድቅ ይሆናል። በተጨማሪም ት/ቤቱ በሚያቀርበው እና በመረጠው ናሙና መሰረት ግዥው ይፈፀማል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ አይደሉም ልዩ ግመገማ አያስፈልጋቸውም ብሎ መስሪያ ቤቱ ያመነባቸውን እቃ በዋጋ በማወዳደር ግዥ ይፈጸማል።
  8. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ሎት 1. ደንብ ልብስ ብር 60,000 (ስልሳ ሺ) ብር፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 45,000 (አርባ አምስት ሺ) ብር ፣ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ 30,000 (ሰላሳ ሺ) ብር ፣ ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች 22,500 (ሀያ ሁለት ሺ አምስት መቶ) ብር ሎት 5. የልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ 26,955 (ሀያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አምስት) ብር ሎት 6. የህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች ፣ 15,000 (አስራ አምስት ሺ) ብር ሎት 7 ቋሚ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ፣ 142,000 (አንድ መቶ አርባ ሁለት ሺ) ብር ሎት 8 የህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች 83,632 (ሰማንያ ሶስት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት) ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቹ ቴክኒካልና ፋይናሻል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተለይቶ ያልቀረበ ሰነድ ከውድድሩ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  9. ተጫራቶች በተጫራቾች የሚሞላውን ማንኛውም መረጃ በጥንቃቄ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሳይሞሉ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
  10. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉት ዕቃ መጠን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ይህን ጨረታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ካላቸው ግለሰቦች ጋር የሚመሳጠሩ ወይም ለመመሳጠር የሚሞከሩ ፤ የጨረታ ሰነዱን ለማሻሻል፤ ለመቀየር እንዲሁም የሌላኛውን ተጫራች ዋጋ መሰረት በማድረግ መሙላት እና ዋና የጨረታ ሰነድና ኮፒ በማንኛውም አግባብ የማይመሳሰል ከሆነ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም በፍሉድ የተነካካ ከሆነ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው ሲፒኦ እንደሚመለስላቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሊወዳደር የሚችለው በአንድ ድርጅት ብቻ ሲሆን በተለያየ ድርጅት ተወዳድሮ ከተገኝ ሙሉ በሙሉ ከውድድሩ ይገለላል። አማራጭ ጨረታ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
  12. የጨረታው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሲሆን የሚሞላው በተቀመጠለት መለኪያ ብቻ ከመለኪያው ውጭ የተሞላ ዋጋ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚመጡ ተጫራች ከአደራጃቸው ወረዳ የድጋፍ ደብዳቤ በተደራጅበት ዘርፍ ጠቅሶ ማምረት በሚችሉት ምርት ወይም በሃገር ውስጥ በሚመረት ምርት ለማከፋፈል ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ሆኖም የሀገር ውስጥ ወይም በራሳቸው ያልተመረተን ምርት ይዘው መወዳደር ከፈለጉ የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ብቻ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ከሆነ በቀጥታ ከውድድሩ በቅድመ ምልመላ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  16. ጨረታ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድም ሆነ ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
  17. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ባንድም በሌላም ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  18. የጨረታ ውጤትን በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ ብቻ ይገለጻል፡፡ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው በቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
  19. የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ገጽ ላይ በማስቀመጥ በሞሉት ሰነድ ላይ ፊርማ ያልተቀመጠ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  20. እቃ አስገብቶ በጀት ቢቆይ ያለምንም ጥያቄ እና ጭቅጭቅ እስኪለቀቅ ለመቆየት ፍቃደኛ የሆነ፡፡

አድራሻ ጎሮ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ፊጋ በሚወሰደው መንገድ 100 ሜትር እንደሄዱ ያገኙናል።

በለሚ/ኩ/ከ/ከተማ የወረዳ 9 ጎሮ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Save Tender