Tender Detail

Tender Details


በአርሲ ዞን የዲከሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ፣ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁ--02/2019

 

በአርሲ ዞን የዲከሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ፣ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም

1.     ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤ እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ)፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸርእቃዎች ለጽዳት እቃዎች፣ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በዲከሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በሂሳብ ቁጥር1000073770231 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር፣ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀነ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ ለአመቺነት በመረጠው ቦታ ይከፈታል፡ጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የጫረታውን ሂደት አይስተጓጉልም።

5.     ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ፤ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ሰእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10.000.00 (አስር ሺህ፤ በአቅራቢያችን በሚገኝ የታወቀ ባንከ በከፍያ ማዘዣ (CP.O.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው::

6.     አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዲክሲስ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ “ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

7.     ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0913349656 0910950695 ይጠይቁ፡፡

 

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

 

Save Tender