Tender Detail

Tender Details


የኤሌክትሮኒክስ፣ ሲሚንቶ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት፣ ጎማ፣ መለዋወጫ ግዥ እና የአጥር ግንባታ (6 ሎት) - በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት2 ሲሚንቶ፣ ሎት3 የመኪና ዘይትና ቅባት ፣ ሎት4 የመኪና ጎማ ፡ ሎት5 የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው አቅራቢዎች እንዲሁም ሎት6 ለሀ/ወ/ ግብርና ጽ/ቤት እና ለሀ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሚሰራው አጥር ግንባታ ስራ ለማሰራት ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸውን GC/BC በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው በተጠየቀው የግዥ አይነትና ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN / ያላቸው
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በውሉ መሰረት ያሸነፉበትን እቃ ግዥ ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ የሚችል ፡፡
  5. ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ፤ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲሚንቶ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት ፣ የመኪና ጎማ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አጥር ግንባታ ስራ በ21 ቀናት እስከ 11፡30 የስራ ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
  6. የጨረታውን ማስከበሪያ የኤሌክትሮኒክስ 40,000/አርባ ሺ ብር/ ፣ ለሲሚንቶ 20,000/ ሃያ ሺ ብር/፣ለመኪና ዘይት ቅባት 10,000/አስር ሺ ብር/፣ለመኪና ጎማ 50,000/ሃምሳ ሺ ብር/፣ለመኪና እቃ ለመለዋወጫ 50,000/ሃምሳ ሺ ብር/ ፤ለአጥር ግንባታ ስራ /20,000/ሃያሺ ብር/በCPO ያስያዙ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመመሪያ ለእያንዳንዱ ሎተጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ አርብ /በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከሚቆይበት እስከ መጨረሻ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ፤ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲሚንቶ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት፣ የመኪና ጎማ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በ16ኛው ቀን አጥር ግንባታ ስራ በ21ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ይታሸጋል የጨረታ ሰነድ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
  10. የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቦታ ግዥ/ን/ብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 ለሀ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ፤ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲሚንቶ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት ፣ የመኪና ጎማ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በ16ኛው ቀን ለአጥር ግንባታ ስራ በ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት እለት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10%የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሴተር እፍ ክሬዲት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ውጤት መሰረት ይሆናል ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Habru Woreda Finance Office seeks suppliers for six lots: electronics, cement, vehicle oil and lubricant, vehicle tires, vehicle spare parts, and fence construction. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration if applicable, and must supply original goods. Fence construction requires GC/BC grade 6 or above.
Save Tender