የምድር ሚዛን (Weighbridge) አቅርቦት፣ ገጠማ እና ሲቪል ሥራዎች (Design & Construct) ለአሰላ፣ አርዳይታ እና ኮፈሌ ሳይቶች (ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/4/2019) - የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/4/2019
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት በሥሩ በሚገኙ በ3 (ሦስት) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም አሰላ፤ አርዳይታ እና ኮፈሌ ሳይቶች የምድር ሚዛን ከነገጠማው እንዲሁም የሲቪል ሥራዎችን (Design & Construct) ጨምሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማቅረብ ሁሉንም (Supply, Installation, testing, Commissioning, training & Civil works (Design & Construct) መስራት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ ቲን፤ እና በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ +251911984467 ወይም +251910567578
ፋክስ 0114-421312
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
