Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Engineering Corporation (የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን)
  • Address ከመገናኛ አደባባይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚወስደው ዋና ቀለበት መንገድ ወደ አደይ አበባ ስታዲዬም (የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል) የሚያስገባው መገንጠያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 118720722
  • Websitehttps://eec.com.et/
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300
  • Bid Securityብር 15,000.00 (CPO ወይም Unconditional Bank Guarantee)
  • opening dateኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. 4:30 ሰዓት
  • Categories Industrial Machinery Provision And Installation , Rent

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፤ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።

Ethiopian Engineering Corporation (የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር EEC/NCB/OP/02/2026

የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ መከራየት በክፍት የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፤ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የግዥ አፈፃፀም ሕጎች እና የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ በተገለጸው የክፍት ጨረታ ሥነ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ይሆናል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ (Unconditional Bank Guarantee) የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ማሰራት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. የዕቃው ዝርዝር እና አገልግሎቶቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (specification) ተያይዟል።
  6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቢያንስ ሶስት ወር የሚጸና መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ ማዘጋጀትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ጨረታው ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጥዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።
  11. ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል።
  12. መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ኢ.ኮ) ሕንጻ 1 ሁለተኛ ፎቅ፡ የግዥ ንብረትና ፋሲሊቲአስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251-924-053-307/+251-11- 897-469/+251-922-346-904

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Engineering Corporation seeks to rent construction machinery for road projects (Adama–Asella, Chefe Donsa, Addis Ababa, Harar) via open tender. Eligible bidders must have a valid business license, VAT registration, and tax compliance proof. Lowest-priced technically compliant bid wins.
Save Tender