የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ጽዳት፣ ሕትመት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስና ስፌት ግዥ (8 ሎት፣ 1/2019) - የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር 1/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ2019 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 ልዩ ልዩ ሕትመቶች
- ሎት 5 ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 7 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ጫማ እና የዳኞች የችሎት ካፓ
- ሎት 8 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት
ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከብር500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት በጥቅል ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በከፊል ወይም ቀንሶ መጫረት አይቻልም።
- የሚገዙትን ዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 30 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር ለጽ/መሣሪያ 8,400 ብር ለቋሚ ቢሮ ዕቃ 4,800 ብር ለጽዳት እቃዎች 1,800 ለሕትመት 1,800 ብር ለቋሚ አላቂ ዕቃዎች 1,200 ብር ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 6,654 ለደንብ ልብስ እና ማሰፊያ 1,800 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ በስማቸው ለደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በማለት ወይም በመስሪያ ቤቱ ሕጋዊ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ በስማቸው ደረሰኝ በማስቆረጥ ከኦርጅናል መጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ብ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ። ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።
- መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ።
- በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116816185 ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት መጠየቅ ይቻላል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Debre Birhan City District Court invites bids for 8 lots: consumable stationery, fixed office supplies, cleaning materials, various printing, miscellaneous fixed/consumable items, electronics, staff uniforms (fabric, shoes, judges' court caps) and uniform sewing. Bidders need a valid 2019 business license, TIN, and VAT registration certificate if purchase exceeds 500,000 birr.
