Tender Detail

Tender Details

  • Company በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Address ሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-84-62-79
  • Website
  • Deadline27 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-27 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Electronics Materials , Camera , Cctv Camera

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለሴኩሪቲ ካሜራ መገጣጠሚያ የሚያገለግሉ እቃዎችና ስካፍሆልዲንግ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለሴኩሪቲ ካሜራ መገጣጠሚያ የሚያገለግሉ እቃዎችና ስካፍሆልዲንግ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተቁ

 

የእቃው አይነት

 

መለኪያ

 

ብዛት

 

ሎት

 

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

 

1

 

4MR IR Bullet Camera

 

በቁጥር

 

84

 

01

 

30,000.00

 

2

 

IR Light

 

በቁጥር

 

80

 

 

 

3

 

Lap Top computer core i7

 

በቁጥር

 

02

 

02

 

10,000.00

 

4

 

Scaffolding

 

በቁጥር

 

01

 

03

 

7,000.00

 

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል።

1.       በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2.       ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባችኋል።

3.       የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው

4.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻው በፖስታ አሽገው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.       ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

6.       በተጫራቾች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት

7.       ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመከላከከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣፣

8.       ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9.       ተጫራቾች የቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10.   ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪያችን በዲዛይን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

11.   የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

12.   ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 30 (ሰላሳ) ተከታታይ የስራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።

13.   ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

14.   አድራሻ፡ ሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ ግድብ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥራችን 0913846279/0910274308 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

Save Tender